Mekinawo App

Follow Up Your Vehicle Expenses

የተሽከርካሪ ወጪዎን በቀላሉ ይከታተሉ


መኪናዎ መተግበሪያ ለሾፌሮችና ለመኪና ባሌቤቶች በተሽከርካሪያቸው ላይ ምን ያህል ወጪ እያወጡበት እንደሆነ ለማወቅ ይረዳቸዋል፡፡ ይህ እንዲሰራ ተጠቃሚዎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ መረጃዎች የተነበበው ኪሎሜትር፣ የነዳጅ እና የሞተር ዘይት ሊትር መጠን እና እነዚህን ለመግዛት የወጣው የገንዘብ መጠን እና ሌሎች ተያያዥ ለተሸከርካሪዎ የወጡ ወጪዎች ናቸው፡፡

መኪናዎ መተግበሪያ የተመዘገቡትን መረጃዎች በማስላት እና በማጠናቀር ምን ያህል የብር መጠን ለተሸከርካሪዎ ነዳጅ፣ ሞተር ዘይት፣ የጋራዥ ጥገና፣ የጎማ ግዥ፣ የጎማ ጥገና፣ ሙሉ እጥበት፣ ከፊል እጥበት እና ሌሎች ወጪዎች እንዳወጡ
. . . እና
ምን ያህል ነዳጅ እና የሞተር ዘይት በመጠነ ሊትር ተሸከርካሪዎ እየተጠቀመ እንደሆነ ሳምንታዊ፣ ወርሀዊ እና ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርብልዎታል፡፡

የኪሎሜትር ንባቡን በተገቢው ሁኔታ ማስገባትዎን በተከታታይ በትክክል ከቀጠሉም መኪናዎ መተግበሪያ ምን ያህል ብር በኪሎሜትር (ብር/ኪሎሜትር) ለተለያዩ የወጪ ምድቦች እንዳወጡ እና ምን ያህል ኪሎሜትር በአንድ ሊትር ነዳጅ እና የሞተር ዘይት (ኪሎሜትር/ሊትር) እንደተጓዘ በተጨማሪም ምን ያህል ሊትር ነዳጅ እና የሞተር ዘይት በአንድ ኪሎሜትር (ሊትር/ኪሎሜትር) ተሽከርካሪዎ እንደተጠቀመ በአማካይ በሳምንት፣ በወር እና በዓመት እንደተጠቀመ ሪፖርት አስልቶ እና አጠናቅሮ ያቀርብልዎታል፡፡

Download Now